አድሜሽ መጽሐፍት ንግድ ስራ የደራሲ ጤንነት ሰጠኝ መጽሐፍት ዋና አከፋፋይ ነው። በተጨማሪም በመጽሐፎቹ ውስጥ የሚገኙ ረቂቅ ሃሳቦችን ትንትኔ በማዘጋጀት በተለያዩ መንገዶች ለሰዎች እንዲደርስ ያደርጋል።

ከታች የሚገኘውን ቁልፍ በመጫን የአድሜሽ መተግበሪያን በስልክዎ አውርድው ይጫኑ።

መተግበሪያው በውስጡ ምን ምን አካቷል?

መጽሐፍት በኢቡክ

ዲጂታል መጽሐፍትን በኢቡክ ያገኛሉ

መጽሐፍት በድምጽ

የመጽሐፍት ትረካዎችን ያገኛሉ

የመጽሐፍት ትንታኔዎች

ትንታኔዎች በድምጽ ወይም በቪድዮ ያገኝሉ

የታተሙ መጽሐፍት

መጽሐፍቱን የሚያገኙባቸውን ድረገጾች ያገኛሉ

የአድሜሽ መተግበሪያን በመገልገል ተጠቃሚ ይሁኑ

ይህ የሞባይል መተግበሪያ ለሃገር ውስጥ አንባቢያን በኢቡክ እና በኦዲዮ ቡክ መልኩ መጽሐፍቶች እንዲደርሷቸው የሚያደርግ ነው።

  • የመፅሐፍት ህትመት ግብአት ወጪ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ከመምጣቱ ጋር በተያያዘ የመፅሐፍትም ዋጋ እጅግ እየጨመረ መጥቷል፡፡ በዚህ የተነሳ አድሜሽ ንግድ ሥራ መፅሐፍቶቹን በህትመት መልክ ከማቅረብ ይልቅ በዲጂታል መልኩ ለአንባቢያን ማቅረቡ ዋጋውን ከመቀነሱ ባሻገር ተደራሽነቱንም ለማስፋት ጠቀሜታው የጎላ ነው፡፡
  • ከዚህ ቀደም ከሃገር ውጪ ለሚገኙ ደንበኞች በአማዞን አማካኝነት የመጽሐፍት ኢቡክ እንዲደርሳቸው መደረጉ ይታወሳል። ነገር ግን ለሃገር ውስጥ ደንበኞች ይህ ምርጫ ስላልነበራቸው የዚህ መተግበሪያ መበልጸግ ለሃገር ውስጥ ደንበኞች መጽሐፍቱ ተደራሽ እንዲሆኑ ያደርጋል።
  • መጽሐፍት ከዚህ ቀደም ወደ ክፍለሃገር ሲላኩ ደንበኞች ጋር እስኪደርስ ድረስ የሚፈጅባቸውን ጊዜ ለመቀነስ ይህን መተግበሪያ እንደ አማራጭ ቢጠቀሙ በቶሎ እጃቸው ላይ እንዲያገኙት ይረዳል።

* ይህን መተግበሪያ ስልክዎ ላይ ለመጫንም ሆነ ከጫኑ በኋላ አጠቃቀሙ ላይ ጥያቄዎች ክሉዎት በሚከተለው ስልክ ቁጥር ይደውሉልን። +(251) 911 616155

ድርጅቱ

አድሜሽ የመጽሐፍት ንግድ ስራ በደራሲና የሃገር በቀል ጥበቦች ተመራማሪ ጤንነት ሰጠኝ በ1999 ዓ.ም ተቋቋመ። ደራሲው ይህን ድርጅት ሲያቋቁም የደረሰባቸውን ሃገር በቀል ሃሳቦች ለብዙኃን የሚደርሱበትን መንገድ የማመቻቸት ራዕይ ስለነበረው ነው።

ባለፉት በርካታ ዓመታትም አድሜሽ የተለያዩ የደራሲ ጤንነት ሰጠኝ መጽሐፍት ለአንባቢያን ሲያቀርብ ቆይቷል። ጤንነት ሰጠኝ የራሱን መጽሐፍቶች እራሱ ባቋቋመው ድርጅት ለአንብቢያን ሲያቀርብ እስከዛሬ ድረስ በተጓዘባቸው መንገዶች ላይ ፈታኝ የሚባሉ ምዕራፎችን በመሻገር ነው።

በነዚህ መጽሐፍት ውስጥ የሚገኙ ሃሳቦች ከሌላ ቦታ ያልተቀዱና ያልተጣቀሱ ሙሉ ለሙሉ የራሱ የደራሲው ሃሳቦች ናቸው። እንዲሁም እነዚህ ሃሳቦች በዓለማችን በሚታወቁ ፍልስፍናዎችም ሆነ ሃይማኖታዊ አስተምህሮቶች ያልተገደቡ ናቸው።

በአድሜሽ መጽሐፍት ንግድ ስራ በዋንኛነት የደራሲ ጤንነት ሰጠኝን መጽሐፍት ዋና አከፋፋይ ነው። በተጨማሪም በመጽሐፎቹ ውስጥ የሚገኙ ረቂቅ ሃሳቦችን ትንትኔ በማዘጋጀት በተለያዩ መንገዶች ለሰዎች እንዲደርስ ያደርጋል። መተግበሪያውን ስልክዎ ላይ በመጫን መጽሐፎቹን ያግኙ።

አድራሻ

ያግኙን

አድራሻ:

ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወርዳ 02

ስልክ:

+(251) 911 729553